ዘላቂነት Sustainability

በዓሚኤል በገና፣ ዘላቂነት ፋሽን አይደለም—ለ3,000 ዓመታት ስንሠራበት የቆየንበት መንገድ ነው። የእኛን መሣሪያዎች ሲመርጡ፣ ተፈጥሯዊ ግብዓቶችን፣ የአገር ውስጥ ባለሙያዎችን እና የኢትዮጵያን መንፈሳዊና ባሕላዊ ቅርስ መጠበቅን ይደግፋሉ። At Amiele Begena, sustainability isn't a trend—it's how we've operated for 3,000 years. By choosing our instruments, you support natural materials, local artisans, and the preservation of Ethiopia's soulful cultural heritage.

የምንጠቀምባቸው ግብዓቶች Our Materials

ተፈጥሮ የሰጠችንን ብቻ በመጠቀም ምድራችንን እናከብራለን። በዎርክሾፓችን ውስጥ ምንም ዓይነት ሰው ሠራሽ ፕላስቲክ ወይም መርዛማ ሙጫዎች አይገኙም። We honor the earth by using only what nature provides. No synthetic plastics or toxic glues are found in our workshop.

  • መሣሪያዎቹ የሚሠሩት በጥንቃቄ ከተመረጠ የዋንዛ እንጨት ነው። Instruments crafted from seasoned Wanza (Cordia Africana) wood.
  • የመሣሪያዎቹ አካል በንጹህ የበሬ ቆዳ ይሸፈናል። Resonators covered with authentic bull hide.
  • አውታሮች (Strings) ከተፈጥሮ የበግ አንጀት የሚፈተሉ ናቸው። Strings hand-spun from natural sheep gut.
  • መሣሪያዎቹን ለመንከባከብ የምንጠቀመው ቅባት ከተፈጥሮ ንብ ሰምና ከሊንሲድ ዘይት ይዘጋጃል። Conditioning wax made from pure beeswax and linseed oil.

የአገር ውስጥ ባለሙያዎችን መደገፍ Supporting Local Artisans

እያንዳንዱ ሽያጭ ባሕላችንን ለሚያስቀጥሉ ባለሙያዎች ቀጥተኛ የገቢ ምንጭ ይሆናል። Every purchase directly impacts the lives of the master craftsmen who keep our traditions alive.

  • 100% በአዲስ አበባ በባለሙያዎች እጅ የሚመረቱ። 100% handmade in our Addis Ababa workshops.
  • ያለ ምንም ደላላ ለባለሙያዎቹ ተገቢውን ክፍያ እንሰጣለን። Fair wages paid directly to craftsmen—no middlemen involved.
  • የባለሙያ ቤተሰቦችንና ማህበረሰቡን መደገፍ። Supporting artisan families and neighborhood stability.
  • ጥንታዊው ጥበብ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ። Ensuring traditional skills are passed to the next generation.

ለረጅም ጊዜ የሚያገለግሉ Built to Last

ጊዜያዊና ጥራት የሌላቸውን መሣሪያዎች አናመርትም። መሣሪያዎቻችን ለትውልድ እንዲያገለግሉ ሆነው የተሠሩ ናቸው። We refuse the "throwaway" culture of modern manufacturing. Our instruments are designed for lifetimes, not seasons.

ጥሩ በገና ወይም ክራር ለትውልድ የሚተላለፍ ቅርስ ነው። አንድ ጊዜ መግዛት የሕይወት ዘመን ዋጋና መንፈሳዊ እርካታን ይሰጣል። A quality Begena or Krar is a heritage piece that improves with age and can be passed down through generations. One purchase represents a lifetime of value and musical companionship.

ባሕላዊ ቅርስን መጠበቅ Cultural Preservation

እነዚህ መሣሪያዎች የኢትዮጵያ የ3,000 ዓመታት የዜማ ጥበብና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅርስ መገለጫዎች ናቸው። These instruments are the heartbeat of Ethiopia's 3,000-year-old musical tradition and Orthodox Christian heritage.

እኛ መሣሪያዎቹን በማቅረብ ጥንታዊው ዕውቀት ሳይጠፋ እንዲቆይ ድልድይ እንሆናለን። ጥንታዊውን ዓለም ከዘመናዊው ጋር እናገናኛለን። By maintaining a marketplace for these crafts, we ensure that the ancient knowledge of instrument making doesn't vanish into history. We are a bridge between the ancient world and the modern one.

ኃላፊነት የተሞላበት አሸሻግ Responsible Packaging

ዘላቂነት እስከ አሸሻግ ሂደታችን ድረስ ይዘልቃል። የፕላስቲክ አጠቃቀምን በመቀነስ መሣሪያዎቹን በጥንቃቄ እንልካለን። Sustainability extends to how we ship. We avoid plastic waste wherever possible while ensuring maximum safety.

እያንዳንዱ መሣሪያ በጥንቃቄ ይታሸጋል። እንደ በገና ያሉ ተሰባሪ መሣሪያዎች ሳይሰበሩ ያሉበት እንዲደርሱ ልዩ ጥበቃ ይደረግላቸዋል። All instruments are carefully hand-packaged. Fragile items like the Begena receive reinforced, protective layers to ensure they arrive in perfect condition without the need for excessive synthetic fillers.

ቃላችን Our Commitment

"ለጥራት፣ ለትክክለኛነትና ለባሕል ኩራት እንቆማለን። ቃላችን ለማህበረሰባችንና ለቅርሳችን ነው—ሁልጊዜም እንደ ድምፃቸው ንጹህና ተፈጥሯዊ የሆኑ መሣሪያዎችን እናቀርባለን።" "We stand for quality, authenticity, and cultural pride. Our commitment is to our community and our heritage—to always provide instruments that are as honest and natural as the sounds they produce."